ስለ እኛ
የአልሙኒየምና ስቲል ስራዎች(መስኮቶች፣ በሮች፣ እና ስቲል ስትራክቸር)ግንባር ቀደም አቅራቢና አምራች ከሆነው ከድርአዲስ ጋር መስራት ይጀምሩ።
ድር አዲስ
ድርአዲስ በአልሙኒየም፣ በብረት እና መስታውት አቅርቦትና መግጠም ስራዎች ላይ የተሠማራ ትልቅ ኩባንያ ነው።
የአዲስ አበባ እምብርት በሆነችው ፒያሳ ላይ የ2500 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ወርክሾፕ፣ በአስርታት የሚቆጠሩ ዘመናዊ የመቁረጫና መገጣጠሚያ መሳሪያዎችና ማሽኖች ይዘን የምንሰራ ስመጥር የአልሙኒየምና ስቲል ባለሞያዎች ነን። ስራዎችን በጊዜ ለማድረስ ብቻ ሳይሆን ጥራት ያላቸው ምርቶችን ለደምበኞቻችን ለማስረከብ ሌት ከቀን እንሰራለን። አሁናዊ የማምረት አቅማችን በወር 950,000 ካሬ ሜትር ነው።
ባህልን እና ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤን ታሳቢ ያደረጉ ስራዎችን መስራት የሚያስችል ጥሩ የጥናት ቡድን አለን። መሣሪያዎቻችን እና ማሽኖቻችን በጣልያን ሃገር ከሚገኙ ስመጥር አቅራቢዎች ያስመጣናቸው ዘመናዊ መሣሪያዎችና ማሽኖች በመሆናቸው አውቶሜሽን ጠርዝ ማሸግ፣ አልሙኒየም ፕሮፋይል መቁረጥና ንጹህ መስታውት ቆረጣን በብቃት እንድናከናውን አስችለውናል።
እንደ ድርጅት የተቋቋምነው ከሦስት ዓመታት በፊት ቢሆንም በግንባታ ስራዎች ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ታማኝነትን አትርፈናል። ስራዎቻችን ሁሉ ሰው ተኮር ናቸው። የጥራት መለኪያችን የደንበኞቻችን እርካታ ነው። ልህቀትን መሠረት አድርጎ መስራት የነገ ብሩህ መንገዳችን ነው። ይህ ከደንበኞቻችን ጋር ለጋራ ግብና ተጠቃሚነት እንድንተጋ አስችሎናል።
ራእይ
ራእያችን ደንበኞቻችን፣ ሰራተኞቻችን እንዲሁም ማህበረሰቡ ላይ ትኩረት በማድረግ ከ10 ዓመታት ባነሰ ጊዜ የአፍሪካ የአልሙኒየም ገበያ ድርሻ በበላይነት መምራት ነው።
ተልእኮ
ተልእኳችን ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችና አገልግሎቶች ለውድ ደንበኞቻችን ማቅረብ ነው። የህብረተሰቡን እና አካባቢ ጥበቃ ግዴታችንን የሞችን አንኳር ነው።
እሴቶችና መርሆዎች
ለጥራት ቁርጠኞች ነን፤ ቃል ከገባነው በላይ እንፈጽማለን። ለደንበኞቻችን እና ፍላጎቶቻቸው አብዝተን እንጨነቃለንና ጥራት የሌለውና ወጥነት የጎደለው ስራ አይጥመንም።
ደንበኞቻችን የሚመርጡን አንድም ታማኝነት የስራችን ካስማዎች መካከል አንዱ ስለሆነ ነው። በችሎታችን፣ በግብራችን እና እሴቶቻችን ሊተማመኑ እንደሚችሉ ያውቃሉ። በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ውስጥ የከበረ ቦታ እንዳላቸው ያውቃሉ።
የስራችንን ውጤት ሊወስኑ የሚችሉ ፈተናዎች ወይም ችግሮች ከማንም ጋር በግልጽ እንወያያለን። ቀጥተኛ እና ግልጽ በመሆን ግንኙነቶቻችን በማዳን እናምናለን።
የእኛ አባላት የሆኑትን፣ ደንበኞቻችን እንዲሁም ማህበረሰባችን ስልጣናቸውን፣ ጾታቸውን፣ እድሚያቸውንና ሌሎች መገለጫዎቻቸውን ግምት ውስጥ ሳናስገባ በማንነታቸው ብቻ እናከብራቸዋለን። ሁሉንም የምናስተናግደው በአክብሮት ነው።
የቀን ተቀን ጥረታችን ወደ ልህቀት መቅረብ ነውና አባሎቻችንን አስፈላጊውን ክህሎትና እውቀት እንዲታጠቁ ማድረግ ላይ እንተጋለን። ለዚህም ሰራተኞች ንባብ ልምዳቸው እንዲዳብር ቤተ መጽሃፍት
ለምን እኛን መምረጥ ይኖርበዎታል?
ምርጡ የምርጡ የአልሙኒዬም እና ስቲል ስትራክቸር አቅራቢና አገልግሎት ሰጪ
ጥራት ተቀዳሚ ግባችን ነውና ለደንበኞቻችን ጥራት ያለው የአልሙኒየምና የብረት ምርቶችን ለማቅረብ ዘመናዊ የጥራት ቁጥጥር ሥርዓት አዘጋጅተናል። እያንዳንዱ የድርአዲስ ቤተሰብ ለጥራት ቁርጠኛ ነው።